Little Life Docs: Science-Based Child Health Child Health,Common Illnesses,Health Promotion,Healthcare Access,Parenting Tips በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis) ምንድነው?

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis) ምንድነው?

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት
The short URL of the present article is: https://childhealthexpert.com/ludw

Sharing is caring!

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ፣  በጨቅላ ወሸፃናት እንዲሁም ታዳጊዎች ላይ የሚከሰት በጣም የተለመደ የቆዳ ሽፍታ ሲሆን ይህም ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ከዳይፐር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው የውጨኛው የቆዳ ክፍሎች  ላይ ሲሆን በዋነኝነትም  መቀመጫዎች፣ የታችኛው የሆድ ክፍል፣  ብልት አካባቢ እና የላይኛው ጭን አካባቢ ላይ በብዛት ይስተዋላል።

Advertisements

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis ) እነማን ላይ ይከሰታል?

ዳይፐር dermatitis እድሜያቸው አንድ ሳምንት ከሞሉ ጨቅላ ህፃናት ጀምሮ ሚከሰት ቢሆንም, ነገር ግን ከፍተኛው የመከሰቱ አጋጣሚ እድሜያቸው ከ9 እስከ 12 ወራት ባሉ ህፃናት ላይ ይበልጥኑ ይስተዋላል። በተሰሩ ጥናቶች መሰረት ከአራት ልጆች መካከል አንዱ ላይ የሚከሰት ሲሆን በፐርሰንት ሲቀመጥ ስርጭቱ ከ7 እስከ 40 በመቶ ይደርሳል ይህም እንደ የዳይፐር አጠቃቀም፣ የሽንት ቤት ሥልጠና፣ የንጽህና አጠባበቅ እና የሕፃናት አስተዳደግ ልምምዶች ሊለያይ ይችላል። 

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis ) ለምን ይከሰታል?

 1. ከመጠን በላይ እርጥበት – በዳይፐር አካባቢ ውስጥ ያለው የእርጥበት መጠን መጨመር በዋነኝነት ሽንትን እና ሰገራን አምቆ ስለሚዝ ውስጣቸው ባለው ኬሚካል አማካኝነት የውጨኛውን የቆዳ ክፍል (stratum corneum)በመጉዳት ለሽፍታው ተጋላጭ ያደርጋል።
 2. ፍትጊያ (Friction) – የውስጠኛውን የቆዳ ክፍል ተጋላጭ በማድረግ ከዳይፐሩ በሚኖራቸው ፍትጊያ ኬሚካሎቹ አልፈው በመግባት የቆዳ መቆጣትን ከማባባስ አልፎ ለኢንፌክሽን ተጋላጭ ያደርጋል።
 3. የቆዳ ፒኤች መጨመር እና የቆዳ ማይክሮባዮም ለውጥ -ሽንት በራሱ አሲዳማ ስለሆነ ቆዳ ላይ ያለውን አሲድ ይበልጥ ከፍ በማድረግ በቆዳው ላይ የሚገኘውን ጠቃሚ ባክቴርያዎች በማጥፋት ጎጂ ለሆኑ ባክቴሪያዎች (S.Aureus, Strep.Pyogens, Candida Albican)፣ ተጋላጭ በማድረግ ችግሩን ያባብሱታል ።
 4. አመጋገብ – ጡት የሚጠቡ ጨቅላ ህጻናት ፎርሙላ  ከሚመገቡት ጨቅላዎች ባነሰ ለዳይፐር dermatitis ተጋላጭ ናቸው።
 5. የቅርብ ጊዜ ተደጋጋሚ  የአንቲባዮቲክ ሕክምና – በቅርብ ጊዜ ሰፋ ያሉ-ስፔክትረም ያላቸውን አንቲባዮቲኮችን መጠቀም ጨቅላ ሕፃናትን ለተቅማጥ እና የፈንገስ ኢንፌክሽን የመያዝ እድላቸውን በመጨመር ለዳይፐር dermatitis አጋላጭ ሊያደርጋቸው ይችላል።
 6. ዳይፐርን በጊዜው አለመቀየር
 7. ለረጅም ጊዜ የቆየ የተቅማጥ ህመም
በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis ) ምልክቶቹ ምንድናቸው?

ቀጥተኛ ግንኙነት ባላቸው የውጨኛው የቆዳ ክፍሎች  ላይ ይህም መቀመጫዎች፣ የታችኛው የሆድ ክፍል፣  ብልት አካባቢ እና የላይኛው ጭን ጨምሮ የሚታይ በጣም የቀላ (Intense Erythema), ሲዳሰስ ሸካራና ከቆዳ ከፋ ያለ (Macules and Papules) ፣እርስ በርሳቸዉ የተያያዙ ትናንሽ ዕብጠት (Coalesce plaques) አንዳንዴም ቅርፊት (Scaling) ሚመስል ነገር ሊኖራቸው ይችላል። 

ከላይ ከተጠቀሱት ችግሮች ጋር ተያይዞም ያለማቋረጥ ማልቀስ ፣ ምቾት ማጣት ፣ለማከክ መሞከር የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ።

በዳይፐር የሚመጣ የቆዳ መቆጣት ወይም ሽፍታ (Diaper Dermatitis) ህክምናው ምንድነው?

የዳይፐር dermatitis ህክምና በዋነኝነት አጠቃላይ የቆዳ እንክብካቤ, ዳይፐር ምርጫ, እና የውጨኛው የቆዳ ክፍል ላይ የሚቀቡ መድሀኒቶችን በዋናነት ይይዛል

 • ዳይፐርን ቶሎ ቶሎ መቀየር – ዳይፐርን ቶሎ ቶሎ መቀየር ቆዳው ከሰገራ እና ከሽንት የሚኖረውን የተራዘመ ጊዜ በመቀነስ ዳይፐር dermatitis የመፈጠሩን ዕድል ይቀንሰዋል። 
 • ያለ ዳይፐር የእረፍት ጊዜያቶችን መስጠት – ዳይፐር dermatitis ያለበት ህጻን ያለ ዳይፐር የእረፍት ጊዜ (ለምሳሌ በቀን ጥቂት ሰዓታት) እንዲቆይ ማድረግ፣ ይህም ቆዳ በቀጥታ ለአየር እንዲጋለጥ ያስችላል።
 • ቀስ ብሎ በለስላሳው ቦታውን ማጽዳት – የዳይፐር ቦታው ለብ ባለ ውሃ እና  በትንሽ መጠን ወይም በፊዚዮሎጂክ ፒኤች ባላቸው ንፅህና መጠበቂያዎች መፀዳት አለበት. እንደ አማራጭ ከሽቶ-ነጻ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ የህጻናት መጥረጊያዎች መጠቀም ይቻላል ነገር ግን በዚህ ወቅት ቆዳው ይበልጥ ሽፍ ካለ አለርጂክ ሊሆንባቸው ስለሚችል ቶሎ ማቆም ያስፈልጋል ፤ ከነዚህም መካከል እንደ methylisothiazolinone ያሉ መከላከያዎች የአለርጂ ንክኪ dermatitis ሊያስከትሉ ይችላሉ።
 • ጎጂ ምርቶችን ማስወገድ -በተለምዶ ቦታው ላይ የሚደረጉ ከበቆሎ የሚሰሩ ግን ለሌላ ጥቅም የሚውሉ Powders ለምሳሌ cornstarch or talcum powder ከፍተኛ የሆነ የመተንፈሻ አካል አደጋ  ሊያመጡ ስለሚችሉ ባንጠቀም ይመከራል። ከነዚህም በተጨማሪ እንደ ቤኪንግ ሶዳ እና ቦሪ አሲድ ዱቄቶች Percutaneous Absorb ስለ ሚደረጉ ሌሎች አካላት ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።
 • የዳይፐር ምርጫ – በሕፃናት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውለው ከሁሉ የተሻለው የዳይፐር ምርጫ አከራካሪ ጉዳይ ነው.ነገር ግን የተራቀቀ የዳይፐር ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሆን ዳይፐር (Disposables ) ዳይፐር dermatitis በሚታከምበት ጊዜ ብንጠቀማቸው ይመከራሉ ምክንያቱም ከፍተኛ የመምጠጥ አቅማቸው ቆዳውን ለሽንት እና ለኬሚካሎች የመጋለጥን ዕድልን  ስለሚቀንስ ነው።
 • ቆዳ ላይ ሚቀቡ መከላከያ ቅባቶች-ከቀላል እስከ መካከለኛ ለሆነ ዳይፐር dermatitis ክሬሞች እንዲሁም ቅባቶች  እንደ መጀመሪያ ሕክምና ያገለግላሉ። እያንዳንዱን ዳይፐር በምንለውጥበት ወቅት እነዚህን ቅባቶች መጠቀም ይኖርብናል። እነዚህ መከላከያዎች በዋነኝነት ኬሚካሎቹ  እንዲሁም እርጥበትን ከቆዳ ጋር እንዳይገናኙ ያደርጋሉ። 

ከነዚህ መከላከያዎች መካከል ፔትሮላተም፣ ዚንክ ኦክሳይድ ወይም ሁለቱንም ያካተቱ ይገኙበታል። አንዳንዶቹ ደግሞ ላኖሊን፣ ፓራፊን ወይም ዲሜቲክኮን (የሲሊኮን ዘይት)  ይይዛሉ።

Waa’ee Shiffee daayipparii irratti dubbisaa!

Views: 27

Leave a Reply

Related Post